በዚህ ዓምድ በማህበረሰባችን የኢሜይል ጥቆማ የተሰበሰቡና መድረኩ ያመነባቸውን የተለያዩ የወቅቱ ዕንቁዎችና ዓርዓያዎቻችን ወገኖችን በአድናቆት ለማመስገንና የሚገባቸውን ክብር ለመስጠት እንወዳለን። መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን በሠፊው ያከተተው ይህ አጭር የዕንቁነትና የመልካም አርዓያነት የዕውቅና መድረክ ስያሜ፣ ማህበርሰቡን በመልካምና ቀናዊ መንፈስ አስፈላጊ ትኩረትና መነቃቃትን ያስገኝለታል ብለን በቅንነት እናምናለን። እርሶም ሆኑ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖችዎ በዚህ ዓውድ የመምረጥና መመረጥ ዕድል ብቻ ሳይሆን፣ በተከታታይ አየመጡ ይህን መድረክ የመጎብኘት ልምድ ጭምር አንዲኖሮዎት ተጋብዝዋል። በዚህም መሠረት በቅድሚያ ስለ ሙሉ ተሳትፎዎ እያመሰገንን ለአስሩም ርዕሶች ዕንቁ ብለው የሚያምኑበትን ከአምስት ዓረፍተ ነገር ከማይበልጥ ማብራራያ ምክንያትዎ ጋር ጥቆማዎ በየወቅቱ አይለየን።