የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥ ሙዚቃ (Community Music of the Season)

community Music or artist
of the season

Tewdros Kasahun
ፍቅር ፈራን | Teddy Afro > Fiker Feran by Ethiopian Music ; Yoftahe's Collection in myp playlist online for free on SoundCloud">

Reason for choice is:

TEDDY AFRO – አርማሽ (ቀና በል) – [New! Official Single 2021] 

https://www.youtube.com/watch?v=PkOstq4GuLk 

ይህ ምርጥ የሙዚቃ ወይም አርቲስት በዚህ መድረክ እጅግ ከፍተኛ ዕውቅና፣ ክብርና ምስጋና ሊያገኝ የበቃበት ምክንያት በወቅታዊ ትርጉሙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያበረክተው ጥቅም በጣም አስፈላጊና ተመራጭ መሆኑ ጎልቶ ስለታመነበት ነው። ይህ ስራ በዘርና ጎሳ ያልተከፋፈለች፣ ሀገራዊ አንድነትን በዜጎች ፍትሃዊ እኩልነትን አረጋግጣ ዕውነተኛና ዘላቂ ሠላም የምታሳይን ኢትዮጵያ የሚናፍቅ ሥራ ስለሆነ ነው።  በተጨማሪም ጥልቅ የሀገር ፍቅር፣ በናፍቆት ተለውሶ የተሰነቀ ተስፋ፣ ስሜት ቀስቃሽና አራማጅ፣  የልበሙሉና ጠንካራ የነፃነት ዓርማን ታሪካዊ የባለቤትነት ይዞታ አስታዋሽነት፣ የወቅቱን አንገት አስደፊ በበሽታ ተይዞ የሚደረግ አድካሚና የረዘመ የሥቃይ ጉዞንም ያስተዋለ ስለሆነም ነው። ቴዲ አፍሮ በዚህ ጉዞ ሕዝቡ አንገት መድፋቱን ትቶ በአንድነት ቀና እንዲል ያሳሰበበት ግሩም ድንቅ ሙዚቃ ነው። መኖር ለአገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ ያለውም ቀና ማለት እስከምን ድረስ መሆኑን ጨምሮ ለመጠቆም ይመስላል። “የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው፣ ቀና በል አሁን፣ ቀና በል ቀና፣ …የጀግኖቹ ልጅ አንተ ነህና፣ ካገር ወዲያ ሞት የለምና፣ ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት፣ ማንም አይገታው የተነሳለት። ቀና በል አሁን ቀና በል ቀና።”  ቴዲ አፍሮ ይህ መድረክ በጣም ያከብርሃል፣ ይወድሃል። በርታ።

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *