Page 10

Page 10 – START

1382 – 1413 በፈቃዱ ዙፋኑን ለልጁ ለቀዳማዊ ቴዎድሮስ የለቀቀው ንጉሥ፣ አጼ ዳዊት፣ በወረብ ወረዳ ውስጥ በራራ የተባለችውን የመካነ ጳጳሳትና የመካነ ነገሥታት የኢትዮጵያ ዋና ከተማ መሠረተ። … ሆኖም ግን፣ በዳዊት ዘመነ መንግሥት የቤተክርስቲያን ውስጣዊ ውዝግብ በፖለቲካ ይዘቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶ ነበር። መኮሳትን አክባሪ የነበርው ቀዳማቂ ዳዊት፣ አንድ ታላቅ የኢየሩሳሌም የምዕመናን ጉዞ አዘጋጅቶ ነበርና፣ ከዚያ መልስ ከክርስቶስ ግማደ መስቀል አንድ ክፋይ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶአል።… ይህም ንጉሥ ዳዊት ከግብፅ ጋር ያደረገው ሰላማዊ ድርድር ያስገኘው ፍሬ ነው። በርሱ ዘመነ መንግሥት ኢትዮጵያ ከክርስቲያናዊው ምዕራብ ጋር ሰፊ ግንኙነት ስለ ነበራት፣ የሀገሪቱን የሥልጣኔ ዕድገት በብዛት ቀይሶታል። 5፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪና ማንቴል ኒያችኮ፣ 2010

የአፄ ዳዊት የቆሮቆሯት በራራ ከተማ፣ የዛሬዋ አዲስ አበባ ላይ የነበረችና በግራኝ አህመድ ሠራዊት የወደመች የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ነበረች። ከግራኝ አህመድ ጦርነት ጅምሮ የመጡ ብዙ ነገሥታት ሥፍራዋን ለትንሳዔ ሲፈልጓትና ዳግማዊ ሚኒልክ ብቻ እንደተሳካላቸው ታሪክ መስክሯል።

በራራ ከተለያዩ የአውሮፓና የእስያ አገሮች የመጡ ሰዎች የሚኖሩባት አለማቀፋዊ ከተማ ነበረች። ብሮኪና ካላብሪያ በራራን በ1482 ዓም በጎበኙበት ጊዜ ብዙ አውሮፓውያን አግኝተው ነበር። አንዳንዶቹ አውሮፓውያን በራራ መኖር የጀመሩት ብሮኪና ካላብሪያ ከተማዋን ከመጎብኘታቸው ከ25 ዓመታት በፊት ማለትም ከዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1434-1468) ዘመነ መንግሥት ጀምሮ ሲሆን ሌሎች ደግሞ በቅርብ ጊዜ ወደከተማዋ የመጡ ነበሩ። አብዛኛዎቹ የመጡት በዘመኑ ታዋቂ ከነበሩት የጣሊያን ከተሞች በተለይም ደግሞ ከቬኒስ ነበር። ቬኒሳውያኑ ጃኮሞ ዲ ጋርዞኒ፣ ጴጥሮስ ዳ ሞንቴ፣ ጁአን ዳርዱኖን ኒቆላዊስ ብራንካሊዮን ሲሆኑ የኔፕልሱ ገብርዔል፣ የጀነዋው ዮሃንስ ዳ ፊስኮ፣ የሮማው ኮላ ዲ ሮሲ፣ የፒድሞንቱ ማቴዎስና የማንቷው ኒቆላዎስ ሁሉም የመጡት ከጣሊያን ነበር። ከጣሊያን በተጨማሪ ከጀርመን፣ ከስፔንና ከፈረንሳይ የመጡም ነበሩ።2

በራራ የኢትዮጵያ የነገሥታቱ እና የጳጳሳቱ ዋና መቀመጫ በመሆን ከዓፄ ዳዊት (1382-1413) ጀምሮ እስከ ዓፄ ልብነ ድንግል (1508-1540) ከመቶ ዓመት በላይ አገልግላለች። ስለከተማዋ ቀጥተኛ ያልሆነ የመጀሪያው የጽሑፍ ምስክር በግንቦት ወር 1375 ዓ ም በዓፄ ንዋየ ማርያም (1372-1382) ዘመነ መንግሥት በዓረብኛ የተፃፈ የጉልት መዝገብ ነው። 105፣ ፣የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪና ማንቴል ኒያችኮ፣ 2010

በራራ መካነ ጳጳሳትና መካነ ነገሥታት ከመሆኗም በተጨማሪ፣ በራራ የባህል፣ የአስተዳዳር እና የፖለቲካ ማዕከል ነበረች። ከሁሉም በላይ ደግሞ የንግድ ከተማ ነበረች። በዚህ ምክንያት በ15ኛው ምዕተ ዓመትና ከዚያም በኋላ ከተለያዩ የአውሮፓ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ እና የእስያ አገሮች የመጡ ነጋዴዎች ከሚኖሩባቸው የኢትዮጵያ ከተሞች በራራ በዋናነት ተጠቃሽ ናት። በወሳኝ የሃይማኖት ጉባዔዎች ለማሳተፍ በተለያዩ ምክንያቶች በራራን ይጎበኙ ነበር። በተጨማሪም በምናኔ ወደኢየሩሳሌም ለሚሄዱ ብዙዎች ኢትዮጵያውያን የጉዞ መነሻቸው በራራ ነበረች። ከግብፅ አገር ጳጳስ ለማስመጣት እንዲሁም ለተለያየ ጉዳይ የመንግሥት ተልዕኮ ተሰጥቶአቸው ወደ አውሮፓ የሚሄዱ አምባሰደሮች እና ልዑካን የጉዞ መነሻቸው በራራ ነበረች።

የበራራን መገኛ ስፍራ ለይቶ ለማመልከት በማገነዘቢያነት የሚረዱ አራት ወሳኝ የታሪክ ምንጮች አሉ። አንደኛውና ዋነኛው የቬኒሳዊው መነኩሴ የፍራ ማውሮ የዓለም ካርታ ነው። ፍራ ማውሮ መልክዓ ምድራዊ መረጃዎችን በመሰብሰብና ካርታ በመሣል ይታወቃል። በተለይ ታዋቂ የሆነበት ሥራው በ1450 ዓ.ም. የሣለው የዓለም ካርታ ነው። ኢትዮጵያንና አፍሪካን ለሚመለከተው የካርታው ክፍል ያገለገሉት ዝርዝር መረጃዎችና ረቂቁን ሥለው የሰጡት የኢትዮጵያ መንኮሳትና አምባሰደሮች ናቸው። በዚህ ካርታና በዙሪያዋ የነበሩ ከተሞች፣ ወንዞችና ገዳማት በትክክለኛ ቦታቸው ላይ ተቀምጠው እናገኛቸዋለን። በካርታው መሠረት የበራራ ትክክለኛ መገኛ የአሁኑ ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ ሲሆን ፣ የከተማው መሀል የዛሬው ኮልፌ ቀራኒዮ መድኃነ ዓለም አካባቢ ነበር።2ተኛው አቢይ የታሪክ ምንጭ የቬኒሳዊው እስክንድር ዞርዚ የመልክዓ ምድራዊና የጉዞ መስመሮች ጥናት ነው። ዞርዚ ስለበራራ ጥናት የጀመረው በ1470 ዓ ም ሲሆን እስከ 1538 ድረስ ስለበራራና ሌሎች ጉዳዮች የሰበሰብውን መረጃ በመፅሐፍ መልክ ሲያዘጋጅ እንደነበረ ይታወቃል። እንደ ፍራ ማውሮ ሁሉ ዞርዚም መረጃውን የሰበሰበው በራራን ጎብኝተው ከተመለሱ አውሮፓውያን እና በራራን መነሻ አድርገው በምናኔ ወደ እየሩሳሌም ፣ ከዚያም ወደተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ከሄዱ ኢትዮጵያውያን ቃለመጠይቅ በማድረግ ነው። … ሶስተኛው ምንጭ የግራኝ አህመድ የዘመቻ ጸሐፊ አረብ ፈቂህ የፃፈው መጽሐፍ ነው። …አራተኛ የከርሰ ምድርና የገፀ ምድር ማስረጃ ነው።26

1402 በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ የባህል፣ የሃይማኖት እና የፖለቲካ የሁለትዮሽ ግንኙነት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። ግንኙነቱም የተጀመረው በኢትዮጵያ አነሳሽነት ነው። በዚሁ ዓመት ዓፄ ዳዊት ለግንኙነቱ ፋና ወጊ፣ ፈር ቀዳጅ የሆነውን የመጀመሪያውን የመንግሥት ልዑክ ወደ ቬኒስ ሪፓብሊክ ላከ። ቀጥለው የነገሱት የኢትዮጵያ መሪዎች ከአውሮፓ ጋር የሚደረገውን ግንኙነት አጠናክረው ቀጠሉበት። በተለያየ ምክንያት ወደ አውሮፓ የሚሄዱት ኢትዮጵያውያንም ቁጥር ጨመረ። … በኢትዮጵያ እና በአውሮፓ ግንኙነት በኢትዮጵያውያን አነሳሽነት ይጀመር እንጂ አውሮፓውያንም የኢትዮጵያን ወዳጅነት በከፍተኛ ደረጃ ይፈልጉት ነበር። ስለዚህም የፈረንሳይቱ ግዛት የቤርይ መስፍን ጴጥሮስ የተባለ የኔፕልስ ተወላጅ እንዲሁም አንድ ፈረንሳዊና አንድ ስፔናዊ ያሉበትን የመጀመሪያ የአውሮፓ ልዑክ በ15ኛው ምዕተ ዓመት የመጀመሪያ ዓመታት (ምናልባትም በአፄ ዳዊት ዘመን) ወደ ኢትዮጵያ ልኮ ነበር። 156

አውሮፓውያን እና ኢትዮጵያውያን አንዳቸው ወደሌላቸው አገር የተጓዙት በአራት አበይት ምክንያቶች ነው። አንደኛው ግለሰቦች ነግዶ ለማትረፍ ካላቸው ከፍተኛ ፍላጎት ነው። ሁለተኛው ምክንያት የመንግሥት ትዕዛዝ ነው። ሦስተኛው የጉዞ ምክንያት ለመንፈሣዊ ልዕልና፣ ለጽድቅ እና ቅድስና ለማግኘት ቤተ ክርስቲያን ለመሣለም የነበረ ፍላጎት ነው። አራተኛውና የመጨረሻው ምክንያት የማወቅ ፍላጎት ነው። 157

በኢትዮጵያ በኩል በመንግሥት ደረጃ የተደረጉ ግንኙነቶች ተቀዳሚ ዓላማ ከአውሮፓ መንግሥታት ዓላማ ጋር ጉልህ ልዩነት ነበራቸው። የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ቅድሚያ የሰጠው ከአውሮፓ ወደኢትዮጵያ የዕደ ጥበብ ሽግግር ማድረግን ነው። ከዕደ ጥበብ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ነገሥታት የአውሮፓን ወዳጅነት የሚፈልጉበት ከደህንነት ጋር የተያያዘ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የማዕከላዊ የኢትዮጵያ መንግሥት በተዳከመ ቁጥር የአዳል ሽፍቶች በተደጋጋሚ ዘረፋ ያደርጉ ነበር። ደካማ ንጉሥ ሥልጣን ሲይዝ የአዳል ሽፍቶች ደቡብ ምዕራብ አረቢያ ባሉ የአረብ መንግሥታት በመታገዝ በተደጋጋሚ ወረራ ስለሚፈጽሙ ኢትዮጵያ የፀጥታ ስጋት ተለይቷት አያውቅም።158

ወደ አውሮፓውያን ስንመጣ የኢትዮጵያን ወዳጅነት የፈለጉበት ዋናው ምክንያት ከአረብና ከኦቶማን ቱርክ መንግሥታት ጋር ለሚያደርጉት ጦርነት ኢትዮጵያ እንድትረዳቸው ስለሚፈልጉ ነው። የክርስትና ሃይማኖት መነሻ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን መልሰው በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ አውሮፓውያን ለመስቀል ጦርነት የሚባለውን ለብዙ ዘመናት ከአረቦች ጋር ተዋግተዋል። ሆኖም ግን የመስቀል ጦርነት የተጠናቀቀው በዓረቦች አሸናፊነት ነው። አውሮፓውያን በ አረቦች በተደጋጋሚ በደረሰባቸው ሽንፈት ምክንያት ከ አውሮፓ ውጪ ካሉ ክርስቲያኖች ወታደራዊ ድጋፍ ማግኘት ይፈልጉ ነበር። 158

በ1145 ስለካህኑ ዮሃንስ የመጀምሪያው የጽሑፍ መረጃ ተገኘ። ይህ አንድ ደብዳቤ በአውሮፓውያን ዕምነት የፈጠረው የካህኑ ዮሃንስ ታሪክ በኢትዮጵያና በአውሮፓ መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር አቢይ ሚና ተጫወተ። በኦቶ ፍሬሲንግ (1114 – 1158) የተጻፈ የታሪክ መጽሐፍ የካህኑ ንጉሥ አገር ከአርመን እና ኢራን በመለስ በእስያ እንደሚገኝ ይዘግባል።ስለካህኑ ንጉሥ ዮሃንስ የአውሮፓውያንን አስተሳሰብ የቀረፀው ለቢዛንቲየሙ ንጉሥ አማኑዔል ኮምንኖስ (1143 – 1180) የተላከ ደብዳቤ ነው።… በኢየሩሳሌም የአኢትዮጵያ ገዳማት መገኘታቸው እና አውሮፓውያንም ይህን ማወቃቸው የካህኑ ንጉሥ ዮሃንስ መገኛ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ነው የሚለው አስተሳሰብ ይበልጡን ተቀባይነት እንዲያገኝ አድረገው። በተጨማሪም ካህኑ ንጉሥ ዮሃንስ የአባይን ወንዝ ማገድ እንድሚችል እና በወታደራዊ ኃይል ከግብጹ መሪ እንደሚበልጥ አውሮፓውያኑ አመኑ። በተለይ ከ1330ዎቹ ጀምሮ ደግሞ አውሮፓውያን ጸሐፊዎችም የካርታ ባለሙያዎችም ካህኑ ንጉሥ ዮሃንስ የኢትዮጵያ ንጉሥ እንደሆነ በግልፅ መጻፍ ጀመሩ። ለምሳሌ ጣሊያናዊው የካርታ ባለሙያ አንጀሊኖ ዱልቸርቶ በ1339 ዓ.ም. ባዘጋጀው ካርታ ማብራሪያ ላይ የኑብያ እና የኢትዮጵያ ክርስቲያኖች በካህኑ ንጉሥ ዮሃንስ ግዛት ሥር እንደሚተዳደሩ በግልፅ አስፍሯል። … በመካከለኛው ዘመን በአውሮፓ ስለካህኑ ዮሃንስ በሰፊው ተሠራጭቶ የነበረው ትርክት አውሮፓውያን ኢትዮጵያን ለማግኘት እንዲተጉ ያደረገ ዋነኛው ምክንያት ነው። በ15 ኛው ምእተ ዓመት አውሮፓውያን ወደ አፍሪካ ያደረጓቸው ጉዞዎች የዚህን ኃያል ንጉሥ አገር ለማግኘት ነበር ለማለት ይቻላል። 159

ከአውሮፓ ውጪ የሚገኘው በጣም ሃብታምና ጠንካራ የክርስቲያን መንግሥት በዘመኑ አውሮፓውያን ዕምነት በተለምዶ ዮሃንስ የሚባል ደግ የሆነ የካህን ንጉሥ የሚመራው የክርስቲያኖች አገር ነው። አውሮፓውያን የካህኑን ንጉሥ ዮሃንስን አገር ፈልገው ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ምንም እንኳ በዘመኑ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ባያውቁትም አውሮፓውያን ወደ ኢትዮጵያ የመጡበት ምክንያት በካህኑ ንጉሥ ዮሃንስ የምትመራዋ ጠንካራ የክርስቲያን አገር ስለመሰለቻቸው ነው። 159

1386 ቀዳማዊ ዳዊት ከሀክ አድ ዲን ፪ኛ ጋር ተዋግቶ ድል ሲያደርግ፣ ባላጋራው በውጊያው ላይ ወድቋል። ሁኖም ይህ ድል ጦርነቱን ሊያቆመው አልቻለም። የሀክ አድ ዲን ተከታይ ሳዓድ አድ ዲን እስላማዊ ኃይሎችን ሁሉ አሰባስቦ በክርስቲያኑ መንግሥት ላይ ወታደር ብቻ ሳይሆን ሕዝብም ጭምር የተሳተፈቡት ዕውነተኛ የቅዱስ ጦርነት ትግል ከፈተ። ይህም እንደገና በንጉሡ ነገሥቱ ድል አድራጊነት ተደመደመ። 66

1429 ከወላስማ ሱልጣናት ጋር ባደረጋቸው ጦርነቶች እና በሌሎችም አያሌ ድሎች ዝና ያተረፈው ንጉሥ ይስሐቅ የጦርነቱን ፍፃሜ ሳያይ፣ በነሐሴ 1429 ከሙስሊሞች ጋር በተደረገ ግጥሚያ ላይ ወደቀ። ይስሐቅ ከሞተ በኋላ ምንም ያህል ታሪካዊ መረጃ ያልተገኘላቸው አያሌ ነገሥታት በኢትዮጵያው ዙፋን ላይ ተቀምጠዋል። ይህ አጫጭር የአልጋ መገለባበጥ የተከሰተው ጦርነቱንም ለረጂም ጊዜ እንዲቋረጥ ያደረገ የወረረሽኝ በመግባቱ ይሁን፣ ወይም ቀዳማዊ ዳዊት ቀድሞ ዙፋን እንዲያስረክብ ያስገደደውና ቀዳማዊ ቴዎድሮስንም ያለ ጊዜው ለሞት ያበቃው ውስጣዊ የተንኮል ሽረባ በመኖሩ ይሁን በውል የሚታወቅ ነገር የለም።

1434 ከሀገሪቱ እጅግ ታላላቅ መሪዎች አንዱ የሆነው ንጉሠ ነገሥት ዘራ ያዕቆብ፣ የዙፋኑ ስሙ ቆስጠንጢኖስ፣ ዙፋን ተረከበ።  ዘራ ያዕቆብ ሥልጣን ለመረከብ ለረጂም ጊዜ ጠብቋል። የሶስት ወንድሞቹንና የሶስት የወንድም ልጆችን ዘመናተ መንግሥት ፍፃሜ አምባ ግሸን ላይ ተቀምጦ በትዕግሥት መጠባበቅ ነበረበት። በመጨረሻ የበሰለ ሙሉ ሰው ሁኖ በ1434 ዓ ም ዙፋን ተቀዳጀ። ገና ከዚያን ሰዓት ጀምሮ ወደ ፊት ስለሚመራው መንግሥት የበሰለ አስተሳሰብ ነበረው፣ ይህም በ2 መሠረተ ሃሳቦች ላይ የቆመ ሲሆን፣ 1) ሥልጣን በጠንካራ ማዕከላዊነት ተዋቅሮ በንጉሠ ነገሥቱ እጅ እንዲያዝና፣ በመላ ሃገሪቱ የሚፀና አንድ የትዕዛዝና የደንቦች ሥርዓት እንዲዘረጋ፣ እና 2) የኢትዮጵያን ወሰን ማስፋትና በሰሜን የሀገሪቱን አቋም ማጠናከር የሚሉ ናቸው። ለ34 ዓመታት በዘለቀው ዘመነ መንግሥቱ ውስጥ፣ ከዓለማዊና ከመንፈሳዊ መኳንንት በኩል የገጠሙትን ከባድ እንቅፋቶች ሁሉ አቸንፎ በጠንካራ የመንፈስ ጽናትና ቁርጠኝነት ዕቅዱን ሥራ ላይ ሊያውለው ችሏል። ያለ ጥርጥር ይህ ንጉሥ ኢትዮጵያ ካፈራቻቸው እጅግ አርቆ ተመልካች ከሆኑት ፖለቲከኞችና ስልተኝነት ከተካኑ ዲፕሎማቶች አንዱ ከመሆኑም በላይ፣ እጅግ ብሩህ አስተሳሰብ ካላቸውና በዕውቀት ከታነፁት ታዋቂ መሪዎች አንዱ ነበር። ከሱ በኋላ የመጡ አያሌ መሪዎች በቀጣዮቹ ምዕተ ዓመታት ውስጥ የርሱን የፖለቲካ አስተሳሰብ ዓርአያቸው አድርገው ተከትለውታል። 69፣ ፣የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪና ማንቴል ኒያችኮ፣ 2010

ከ1434 እስከ 1454 ባሉት ዓመታት ውስጥ ዘራ ይዕቆብ የፖለቲካ ግቦችን ሁሉ ሥራ ላይ አውሏቸዋል፣ ወይም መስመር አሲዟቸዋል። በአንድ በኩል ለሰሜኑ ግዛት አስተዳዳሪ ከሌሎቹ ጠቅላይ ገዥዎች ሁሉ የላቀ ክብደትና ደረጃ ያጎናጸፈ ሥልጣንና ክብርን በመስጠት፣ በሌላው በኩል ደግሞ በዚያ ያለውን የክህነት ዘርፍ አቋም በማጠናከር ሥልጣኑን በሰሜን እስከ ባሕር ዳርቻ ድረስ አስፋፍቷል። የተማከለ አስተዳደራዊ ሥርዓት በመዘርጋትና ፣ እንዲሁም አለሁ አለሁ የሚሉትን የቀበሌ ባላባቶች ሥልጣን በመቀንጠቅ መንግሥቱን አንድ አድርጓል። የኢትዮጵያው ቤተ ክርስቲያን አንድ ወጥ የሆነ ተቋም እንዲሆንና ግልፅ የሆነ ርዕዮተ ዓለም እንዲኖረው አድርጓል። በዚህም ተቋም አማካይነት የተናቁት ማህበራተ ሰብ ባህላዊና ፖለቲካዊ አቋም ከፍ እንዲል አድርጓል። በዚሁ ጊዜ ውስጥ ከእስላም ሱልጣናት ጋር የነበረውን ከ100 ዓመት በላይ የዘለቀ ጦርነት አንፀባራቂ በሆነ ድል በንጉሣዊው መንግሥት የበላይነት እንዲደመደም አድርጓል። 82 ፣የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪና ማንቴል ኒያችኮ፣ 2010

1468 ዘራ ያዕቆብ ነሐሴ 26 1468 ዓ.ም. ደብረ ብርሃን ላይ አረፈ። አንድ የሆነችና በንጉሠ ነገሥቱ ፍፁማዊ አገዛዝ የጸናች የምትመስል ኢትዮጵያን ለልጁ ሊያስረክቡ ችሏል። (ግን) የአዲሱ መሪ የመጀምሪያ እርምጃ አባቱ የሠራውን ሁሉ ማፍረስ ሆነ። ንጉሥ በዕደ ማርያም የዘራ ያዕቆብ ልጅ ነሐሴ 26 ቀን 1468 በዕለተ ሰንበት ከቀኑ በ9 ሰዓት ላይ በሀያ ዐመት ዕድሜው በኢትዮጵያ ዙፋን ላይ ተቀመጠ። 86፣ ፣የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪና ማንቴል ኒያችኮ፣ 2010

ንጉሠ ነግሥት በዕደ ማርያም፣ የንጉሠ ነግሥት ዘራ ያዕቆብ ልጅ፣ የአባቱን ፍፁማዊ የንጉሠ ነግሥት የተማከለ ሥልጣን የመፍጠር ሙከራን እንዲዳከም አደርጓል። … የሟቹን ንጉሠ ነገሥት የተማከለ ሥልጣን ፖሊሲ ይቃወም ለነበረው ሁሉ የምህረት አዋጅ አስነገረ። እንዲሁም በዚያው ዕለት በሁሉም ጠቅላይ ግዛቶች የጥንት ማዕረጎች ተመልሰው እንዲፀኑና፣ አብዛኞቹ ዘራ ያዕቆብ የፈጠራቸው ሹመቶች እንዲታጠፉ አደረገ። በንጉሠ ነግሥቱ የተሾሙትንና በሱ ፈቃድ አዳሪ የነበሩትን አስተዳዳሪዎች አንስቶ፣ በምትካቸው በብዙ ጥረት ተሰሚነት እንዲያጡ የተደረጉትን የቀበሌ ባላባቶች ወደየዙፋናቸው መለሳቸው። የአዲሱ ንጉሠ ነገሥት አስተሳሰብ፣ እያንዳንዱ አካባቢና እያንዳንዱ ማህበረሰብ ለሱ ግብር እስካስገባ ድረስ ውስጣዊ ነፃነት ሊኖረው ይገባል የሚል ነው። በዕደ ማርያም ለእያንዳንዱ ቀበሌ ነፃነቱን ሰጠው፣ የየቀበሌው ሕዝብ በምንም መንገድ አጠቃላይና አንድ ወጥ አስተዳደር፣ ወይም አንድ ወጥ ሥነ ምግባር ተከተል ሳይባል እንደየቀበሌው ልማድ የመኖር መብቱን ፈቀደለት። በ1445 ዓ.ም. ከእስላማዊው የወላስማ የገዥ ቤት ደረጃ ወርደው ለዘለቄታው በክርስቲያኑ ንጉሣዊ መንግሥት ውስጥ ታቅፈው የነበሩት የይፋት ገዥዎች በቀድሞ የማዕረግ ስማቸው ወላስማ ተብለው እንዲጠሩ ተፈቀደላቸው። 86-87

በንጉሠ ነገሥቱ ዘራ ያዕቆብ አዲስ የተፈጠረው የራቅ ማሠሬ ሹመት ተነሳ። የአማራ፣ የሸዋ የዳሞት ጠቅላይ አስተዳዳሪዎች ጸሐፌ ላም የሚል የማዕረግ ስም ይሰጣቸዋል። የአንጎት፣ የትግሬና የቅዳ አስተዳዳሪዎች ባሕር ነጋሽ ይባላሉ። የሀዲያ፣ የገንዝና የደዋሮ አስተዳዳሪዎች ገራድ ይባላሉ። የግድም አስተዳዳሪ አካፀን፣ የገኝ አስተዳዳሪ ንጉሥ፣ የጎጃም አስተዳዳሪ ነጋሽ የሚል የማዕረግ ስም አላቸው። 87

1445 በዚህ ወቅት ላይ የተጠናከሩት የደቡባዊ ምሥራቅ ሙስሊማዊ ኃይሎች አደጋ እያደገ መጣ። የይፋት ሱልጣን መውደቅ፣ ዋናው የእስላም ኃይል አዳል ላይ እንዲቋጠርና ፣ በሐረር አካባቢ አዲስ ማዕከል እንዲፈጠር መንስዔ ሁኗል። ይህ ወደ ደቡባዊ ምሥራቅ አቅጣጫ የተደረገው ሽግሽግ በአፍሪካ አህጉር ውስጥ ካሉ የእስላም ቀበሌዎችና፣ እንዲሁም የዘይላን ወደብ ማዕከል ካደረጉ የጠረፍ ግዛቶች ጋር ግንኙነት እንዲያጠናክሩ ዕድል ሰጣቸው፣ የደቡብ ምሥራቅ አፍሪካ እስላማዊ አካባቢዎች አንድ ሁነው ቀጥታ ከመላው የእስላም ዓላም ጋር እንዲተሳሰሩ አስችሏቸዋል። አሁን ዘይላን ከሸዋ ጋር በሚያገናኘው የንግድ መስመር ላይ ማተኮር ያዙ። 97

በንጉሥ በዕደ ማርያም ዘመነ መንግሥት መጀመሪያ ዓመታት ላይ፣ የአዲሱ ሱልጣን ሞሐመድ ቤን በድላይ፣ ለግዛቱ የጥፋት ምንጭ ሁኖ የሚኖረው የሸዋ ወረራ የሚቆም ከሆነ እገብርልሃለሁ ሲል የድርድር ሀሳብ አቀረበ። ንጉሠ ነገሥቱ ይህን ሀሳብ የተቀበለው ቢሆንም፣ ገና ዘመነ መንግሥቱ ከማለቁ በፊት፣ ጉልበት የሚሰማው አዳል በንጉሠ ነገሥቱ የድንበር ወረዳዎች ላይ ጥቃት መፈፀም ጀምሯል። በዚህን ጊዜ ንጉሡ በእስላሞች ላይ ሠራዊት ለማዝመት ወሰነ። 97

የኢትዮጵያ መሪዎች የተለየ ትኩረት የሚሰጡት በተለይ በዚያን ጊዜ የመንግሥቱ ማዕከል ለሆነው ለሸዋ ጠቅላይ ግዛትና፣ ከኤኮኖሚያዊ ጥቅም አኳያ ጠቃሚ ለሆኑት እንደ ሀዲያ፣ ፈጠጋርና ወጅ ላሉት የእስላም አካባቢዎች ነበር። እነዚህ ጠቅላይ ግዛቶች ለመጠበቅ የግድ ጦር ማስፈር አስፈላጊ ነበር። ከዚህ በተለየ መንገድ የኢትዮጵያ መሪዎችየነዚህን ፖለቲካዊ አቋም ለማቃናት ሲሉ፣ ቤተሰቦቻቸውን በዚያ ከሚገኙ የገራድ ሥርወ ገዥዎች ጋር በጋብቻ ያስተሳስሩ ነበር። ንግሥት እሌኒና የበዕደ ማርያሚቱ ቀኝ ባልቲሀት ከእስላማዊ የባላባት ቤት የሚወሰዱ ናቸው። … የንጉሠ ነገሥቱ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሁሉ የተፈለገውን ውጤት ሳያስገኝ ቀርቶ፣ የይፋት፣ የፈጠጋር፣ የደዋሮ፣ የሀዲያ፣ የወጅና የባሌ ቀበሌዎች፣ ለወደፊት በኢትዮጵያ ላይ የተጋረጠ አደጋ ሆኑ። በናኦድ ዘመነ መንግሥት (1494-1508) ሞሐመዳዊ ወገኖች ባሌን ከንጉሣዊው መንግሥት አካልነት ገንጥለው ለማውጣት እጅግ ከፍተኛ ጥረት አድርገው ነበር። 98

Page 10 –END

Comments are closed.