.የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥ ተነባቢ መፅሃፍ (Community Recommended Book of the Season)

የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥ ተነባቢ መፅሃፍ (Community Recommended Book
of the season)

በራራ - ቀዳሚት አዲስ አበባ
(1400 - 1887ዓ.ም.) እድገት፣ ውድመት እና ዳግም ልደት
ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ

ይህ መፅሃፍ የተመረጠበት ምክንያት: የዛሬው ትውልድ የተለያዩ አገራዊ አንድነትን ለሚቃረኑ ሃሰተኛ ታሪክና ትርክቶች የተጋለጠ በመሆኑ ይህ መፅሃፍ ግን እጅግ አስፈላጊና ሃቀኛ ታሪክን ለትውልዱ በሚያስገርም መልኩ የቀዳማዊት አዲስ አበባን ታሪክ በማስረጃ ያቀርባል። ይህ መፅሀፍ ዛሬ በኢትዮጵያ የጎሳ ብሔርተኛ ኃይሎች ያመጡትን የአዲስ አበባ ከተማን የባለቤትነት ጥያቄ በልዩ ዓይን ለማየትና ለመመርመር ይረዳል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን በጣም በሚደንቅ ደረጃ በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጀ ታሪካዊ መፅሃፍ፣ “ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ” በሚል እንደ አዲስ ታሪካዊ ማስረጃ በመውሰድ ስለ አዲስ አበባ ከተማ ታሪክ የራሱን ግንዛቤና ድምዳሜ ያገኝበታል። ደራሲው፣ ዶክተር ሃብታሙ መንግሥቴ፣  ይህን ታላቅ ታሪካዊ ማስረጃ የሆነ መፅሃፍን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያበረክቱ ለወቅታዊ ፈተናዎቻችን መፍትሔ ለማበርከት ስለሆነ ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል።

 

All of the below was taken from the Amazon online marketplace for your purchase convenience:

Barara (Addis Ababa’s Predecessor): Foundation, Growth, Destruction and Rebirth (1400-1887) (Amharic Edition) Paperback – March 9, 2020

by Habtamu Tegegne (Author)

This book explores the development, destruction, and re-establishment of Ethiopia s lost medieval capital of Bärara, whose enormous significance has scarcely been touched upon by modern historians. By exploring and revealing the city s importance as a major ecclesiastical and political capital, the book challenges traditional historiography that until now undermined the significance of medieval Ethiopian urban culture. While Bärara is far from unknown to scholars, only this book historicizes the city by situating its role within the much larger political and cultural contexts of Ethiopian and world history, contesting the assumption that the Ethiopian middle ages featured unsophisticated roving capitals that functioned as such only while local or regional rulers were in residence. While the book s central focus is Bärara, it is broadly conceived as an ambitious reinterpretation of Ethiopian history during the medieval and early modern periods. The book uses the city s development, destruction, rediscovery and refoundation as a lens through which to view larger developments in Ethiopian history notably the political and cultural regeneration of the early Solomonic era (1270-1529), Ahmad Ibrahim s (1529-1543) short-term empire and its long-term consequences, and the Ethiopian reconquests and reconstructions of the sixteenth and seventeenth centuries which extended into the end of the nineteenth century. By reading modern Addis Ababa as Bärara reborn, the book argues that the medieval history of Bärara was a crucial factor in founding Ethiopia s modern capital, as well as motivating military campaigns of Emperor Menilek II (r. 1889-1913) to eastern, southern, and western Ethiopia. The detailed research in this book shows that the significance of Bärara in medieval Ethiopia was a greatly neglected topic that could potentially shed new and revealing light on recurring themes of Ethiopian history. The book will add depth and a new layer of meaning to the very contentious political debate concerning contemporary Addis Ababa.


 

የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥና ታታሪ ተማሪ (Community Excellent Student of the Season)

Community Execellent Student of the season

Workneh Fola Jano

የተመረጠበት ምክንያት (Reason for choice is):

ወርቅነህ የተመረጠበት ምክንያት ዛሬ በኢትዮጵያ የሚገኝ ማንኛውም ወጣት ከየትኛውም የኑሮ ደረጃና ሥፍራ ተነስቶ ከዓለማችን ዝናን ያተረፈ የአሜሪካ ዩንቨርሲቲ ገብቶ የመማር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ማሳያ ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ግን ጠንካራና የበሰለ ስብዕና እና አመለካከት በመያዝ በታታሪ ሰራተኛነት ለዕውቀትና ጥበብ ከፍተኛ ዝንባሌ ሲኖር ጭምር ነው። ዓለም አቀፋዊ ጥራትና ብቃት ያለው ትምህርት ቤት ለመግባት ዓለም አቀፋዊ የጥራትና ብቃት ደረጃ ያለው አመለካከትና ብስለትን ይጠይቃል። ወጣት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ራሳቸውን እንደ ወርቅነህ በፍፁም ታታሪ ሰራተኛነትና ከፍተኛ የዕውቀት ፍቅርን አዳብረው በትጋት የትምህርታቸውን ዓላማ ቢሰሩብት ተመሳሳይ ዕድል ይገጥማቸዋል ብሎ ይህ መድረክ ያምናል። የወርቅነህን መንገድ ከዚህ በታች ያለውን ዩቲዩብ በማጫወት ይመለከቱ ዘንድ ተጋብዘዋል። እስከ አሁን በመጣበት መንገድ የወቅቱ ዓርአያችን አድርገን የመረጥንህ ወጣት ወርቅነህ እናኮራብሃለን፣ አናከብርሃለን፣ እንወድሃለን፣ በርታ።

https://www.youtube.com/watch?v=jDXiMaeozRg

የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥና ታታሪ ሠራተኛ ወይም ድርጅት ወይም የፈጠራ ውጤት ባለቤት (Community Best Working Person Or Inventor of the Season)

Eshetu Melese

የተመረጠበት ምክንያት (Reason for choice):
እስከ አሁን በመጣበት መንገድ እሸቱ መለሰ ለዘመናችን ትውልድ እጅግ በጣም ተወዳጅ፣ ስኬታማ፣ ዕንቁና መልካም ዓርአያ የሆነ ዜጋ ነው። እሸቱ ዛሬም ወጣቱ ትውልድ እንዴት በራስ ጥረትና ብልጠት ራሱን ከድህነትና ሥራ አጥነት አንስቶ ለከፍተኛ ስኬታማ ህይወት ማብቃት እንደሚቻል ያሳየ ዕንቁና መልካም ዓርአያ ዜጋ ነው። እሸቱ ዶንኪ ቲዩብ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤት ሲሆን በቀልድ መድረክ ሥራዎቹና ሥጦታው አስፈላጊ አገራዊ አገልግሎቶችን በማበርከት ላይ ይገኛል። እሸቱ መልካም ግለሰባዊ ሥነባህርያትና ምርጥ ኢትዮጵያዊ ዕሴቶችን ራሱ ተላብሶ ሥራዎቹ ላይ በትኩረት ተመሳሳይ ዕሴቶችን በማህበረሰቡ ዘንድ በማጠናከርና በመንከባከብ ላይ ሲሰራ ይታያል። ሕዝብና ሃገርን ከልብ በቀናዊ መንፈስ ሲያገለግሉም ግላዊ ብልፅግናና ደስታ ማግኘት እንደሚቻል የወቅቱ ዓር አያችን አድርገን የመረጥነውን አቶ እሸቱ መለሰ ጥሩ ማሳያ ነው ብሎ ይህ መድረክ ያምናል። 
እሽቱ መለሰ እናከብርሃለን፣ እንወድሃለን፣ በርታ።  
According to the You tube description page of Donkey tube: Donkey tube is a Media Company that mainly focuses on echoing a voice to the voiceless, donkey tube has been working hard in raising awareness in different sociological matters for the last 3 and more years. holding more than 40 employees in it’s realm, this media company has been the reason for the change of so many lives throughout the country. Comedian Eshetu Melese meticulously brought this company from the start with his colleagues. Comedian Eshetu is an Ethiopian based Standup Comedian, Entrepreneur and philanthropist who devoted his life in to making this world a better place. he created stages and made his own voice heard by so many people raising awareness by disguising it via humor and comedy.

                https://www.youtube.com/@comedianeshetu/about 

 

 
Daniel Yohannes

የወቅቱ የማህበረሰባችንብሩህ የማህበራዊሚዲያ ወይም አስተዋፅዖ አቅራቢ ዜጋ (Best Social Media or Model Contributor of the Season)

community social media contributor
of the season

Dr. Daniel Yohannes
Daniel Yohannes

Reason for choice is:

ለሠው ልጅ ጤና ትልቁና አንደኛ ደረጃው ሃብት ነው። ሌሎች የሃብትና ኃይል ዓይነቶች ተርፈው ቢገኙ፣ የሠው ልጅ የጤና ጉድለት ከተገኘበት የኑሮው ጥራት ላይነሳ ወዳቂ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ አካላዊ ጤናን መንከባከብና በጥሩ ደረጃ ጠብቆ መያዝ ዕለታዊ ተግባር ሊሆን ይገባል። ዶ/ር ዳንዔል ዮሃንስ ከዚህ አኳያ ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዕለታዊና አካላዊ ጤንነታቸውን እንዴት በጥሩ ደረጃ መያዝ እንደሚችሉ ሳይንሳዊ ዘዴና ዕውቀታቸውን በዩ ቲዩብ “የኔ ጤና” በሚል ማህበረሰባቸውን በከፍተኛ ደረጃ በመጥቀም ላይ ይገኛሉ። ዶ/ር ዳንዔል እጅግ ተመራጭና አስፈላጊ ሥራ ለማህበረሰባችን እያቀረቡ ስለሆነ ይህ መድረክ ታላቅ ክብርና ምሥጋና ያቀርብልዎታል። 

የኔ ጤና – Yene Tena [@yenetena 347K subscribers 266 videos] 

Dr.Daniel Yohannes (Dr.Dany) is clinical pharmacist , functional nutritionist and healthy life style strategist. He is working as pharmacy director in his work place . 

https://www.youtube.com/@yenetena/videos  

Description: Dr.Daniel Yohannes (Dr.Dany) is a clinical pharmacist, functional nutritionist and healthy lifestyle strategist. He is working as pharmacy director in his workplace. Using Credible research, scientific common sense and extensive medication therapy training, daily helping many patients to live a healthy, full and satisfied life. This channel will provide simplified health related topics from weight loss, evidence-based nutrition (with cooking demo), drug therapy options, drug interactions, sleep and so much more. Every week new content will be uploaded, do not forget to subscribe to get all the content created on this channel. Let this Channel add value to stay healthy one day at a time. all comments and questions welcome to help you more. 

Source: All the above was directly taken from “Yene Tena” YouTube home page. 
Listen to ቴዎድሮስ ካሳሁን > ፍቅር ፈራን | Teddy Afro > Fiker Feran by Ethiopian  Music ; Yoftahe's Collection in myp playlist online for free on SoundCloud

የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥ ሙዚቃ (Community Music of the Season)

community Music or artist
of the season

Tewdros Kasahun
ፍቅር ፈራን | Teddy Afro > Fiker Feran by Ethiopian Music ; Yoftahe's Collection in myp playlist online for free on SoundCloud">

Reason for choice is:

TEDDY AFRO – አርማሽ (ቀና በል) – [New! Official Single 2021] 

https://www.youtube.com/watch?v=PkOstq4GuLk 

ይህ ምርጥ የሙዚቃ ወይም አርቲስት በዚህ መድረክ እጅግ ከፍተኛ ዕውቅና፣ ክብርና ምስጋና ሊያገኝ የበቃበት ምክንያት በወቅታዊ ትርጉሙ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያበረክተው ጥቅም በጣም አስፈላጊና ተመራጭ መሆኑ ጎልቶ ስለታመነበት ነው። ይህ ስራ በዘርና ጎሳ ያልተከፋፈለች፣ ሀገራዊ አንድነትን በዜጎች ፍትሃዊ እኩልነትን አረጋግጣ ዕውነተኛና ዘላቂ ሠላም የምታሳይን ኢትዮጵያ የሚናፍቅ ሥራ ስለሆነ ነው።  በተጨማሪም ጥልቅ የሀገር ፍቅር፣ በናፍቆት ተለውሶ የተሰነቀ ተስፋ፣ ስሜት ቀስቃሽና አራማጅ፣  የልበሙሉና ጠንካራ የነፃነት ዓርማን ታሪካዊ የባለቤትነት ይዞታ አስታዋሽነት፣ የወቅቱን አንገት አስደፊ በበሽታ ተይዞ የሚደረግ አድካሚና የረዘመ የሥቃይ ጉዞንም ያስተዋለ ስለሆነም ነው። ቴዲ አፍሮ በዚህ ጉዞ ሕዝቡ አንገት መድፋቱን ትቶ በአንድነት ቀና እንዲል ያሳሰበበት ግሩም ድንቅ ሙዚቃ ነው። መኖር ለአገር ሲሆን ሞትም አያስፈራ ያለውም ቀና ማለት እስከምን ድረስ መሆኑን ጨምሮ ለመጠቆም ይመስላል። “የኢትዮጵያዊነት አሁን ነው ተራው፣ ቀና በል አሁን፣ ቀና በል ቀና፣ …የጀግኖቹ ልጅ አንተ ነህና፣ ካገር ወዲያ ሞት የለምና፣ ዝም ያለ መስሎ ኢትዮጵያዊነት፣ ማንም አይገታው የተነሳለት። ቀና በል አሁን ቀና በል ቀና።”  ቴዲ አፍሮ ይህ መድረክ በጣም ያከብርሃል፣ ይወድሃል። በርታ።