የማህበረሰባችን በወቅታዊ ጠቃሚነቱ ምርጥ ጥቅስ (Community Best Useful Quote of the Season)

community contemporary quote
of the season

" You cannot hope to build a better world without improving
the individuals. " By Marie Curie

Reason for choice is:

Ethiopia poverty

ይህ ጥቅስ የተመረጠበት ምክንያት ዛሬ በኢትዮጵያ ውስጥ፣ ሀገርና ከተማ እንገነባለን በሚል፣ ቢያንስ የጊዜያዊ ምትክ መጠለያን አማራጭ ማቅረብን በቅድሚያ ታሳቢ ያላደረገ፣ ሰብዓዊ ርህራሄን፣ ማህበራዊ ኃላፊነትና መንግሥታዊ ተጠያቂነት በጎደለው መልክ፣ የግለሰብ ዜጋን ህይወት የማፍረስና መበተን ሥራ በዕቅድና የዕድገት ተስፋ ስም ሲሰራ ይታያል። ይህ የቅደም ተከተል መዛባት ነው። በእርግጥም ቅደም ተከተሉ በዚህ መልክ ተዛብቶ ፍትሃዊ፣ ሰብዓዊና፣ ማህበራዊ  ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ሀገር ልንገነባ ስንሞክር ደግሞ እጅግ አሳዛኝ ዋጋ ያስከፍላል። ጥቅሱ የወቅቱን መንግሥታዊ አስተሳሰብንና የቀዳማዊ ትኩረት መዛባት ችግርን ፍንትው አድርጎ በንፅፅር ስለሚያሳይ ተመራጭነቱ ጎልቶ ታይቷል። ይህ መድረክም ፍትሃዊ ዕድገትን በኢትዮጵያ ለማምጣት የብልፅግና ግንባታው ከግለሰብ ዜጋ መጀመሩ ቅድሚያ የሚሠጠው መርህ መሆኑን በቀላሉ ይረዳል።

Add a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *