Eshetu Melese
የተመረጠበት ምክንያት (Reason for choice):
እስከ አሁን በመጣበት መንገድ እሸቱ መለሰ ለዘመናችን ትውልድ እጅግ በጣም ተወዳጅ፣ ስኬታማ፣ ዕንቁና መልካም ዓርአያ የሆነ ዜጋ ነው። እሸቱ ዛሬም ወጣቱ ትውልድ እንዴት በራስ ጥረትና ብልጠት ራሱን ከድህነትና ሥራ አጥነት አንስቶ ለከፍተኛ ስኬታማ ህይወት ማብቃት እንደሚቻል ያሳየ ዕንቁና መልካም ዓርአያ ዜጋ ነው። እሸቱ ዶንኪ ቲዩብ የተሰኘው የማህበራዊ ሚዲያ ባለቤት ሲሆን በቀልድ መድረክ ሥራዎቹና ሥጦታው አስፈላጊ አገራዊ አገልግሎቶችን በማበርከት ላይ ይገኛል። እሸቱ መልካም ግለሰባዊ ሥነባህርያትና ምርጥ ኢትዮጵያዊ ዕሴቶችን ራሱ ተላብሶ ሥራዎቹ ላይ በትኩረት ተመሳሳይ ዕሴቶችን በማህበረሰቡ ዘንድ በማጠናከርና በመንከባከብ ላይ ሲሰራ ይታያል። ሕዝብና ሃገርን ከልብ በቀናዊ መንፈስ ሲያገለግሉም ግላዊ ብልፅግናና ደስታ ማግኘት እንደሚቻል የወቅቱ ዓር አያችን አድርገን የመረጥነውን አቶ እሸቱ መለሰ ጥሩ ማሳያ ነው ብሎ ይህ መድረክ ያምናል።
እሽቱ መለሰ እናከብርሃለን፣ እንወድሃለን፣ በርታ።
According to the You tube description page of Donkey tube: Donkey tube is a Media Company that mainly focuses on echoing a voice to the voiceless, donkey tube has been working hard in raising awareness in different sociological matters for the last 3 and more years. holding more than 40 employees in it’s realm, this media company has been the reason for the change of so many lives throughout the country. Comedian Eshetu Melese meticulously brought this company from the start with his colleagues. Comedian Eshetu is an Ethiopian based Standup Comedian, Entrepreneur and philanthropist who devoted his life in to making this world a better place. he created stages and made his own voice heard by so many people raising awareness by disguising it via humor and comedy.
https://www.youtube.com/@comedianeshetu/about
Add a Comment