የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥና ታታሪ ተማሪ (Community Excellent Student of the Season) Community Execellent Student of the season Workneh Fola Jano የተመረጠበት ምክንያት (Reason for choice is): ወርቅነህ የተመረጠበት ምክንያት ዛሬ በኢትዮጵያ የሚገኝ ማንኛውም ወጣት ከየትኛውም የኑሮ ደረጃና ሥፍራ ተነስቶ ከዓለማችን ዝናን ያተረፈ የአሜሪካ ዩንቨርሲቲ ገብቶ የመማር ዕድል ሊኖር እንደሚችል ማሳያ ስለሆነ ነው። ይህ ማለት ግን ጠንካራና የበሰለ ስብዕና እና አመለካከት በመያዝ በታታሪ ሰራተኛነት ለዕውቀትና ጥበብ ከፍተኛ ዝንባሌ ሲኖር ጭምር ነው። ዓለም አቀፋዊ ጥራትና ብቃት ያለው ትምህርት ቤት ለመግባት ዓለም አቀፋዊ የጥራትና ብቃት ደረጃ ያለው አመለካከትና ብስለትን ይጠይቃል። ወጣት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ራሳቸውን እንደ ወርቅነህ በፍፁም ታታሪ ሰራተኛነትና ከፍተኛ የዕውቀት ፍቅርን አዳብረው በትጋት የትምህርታቸውን ዓላማ ቢሰሩብት ተመሳሳይ ዕድል ይገጥማቸዋል ብሎ ይህ መድረክ ያምናል። የወርቅነህን መንገድ ከዚህ በታች ያለውን ዩቲዩብ በማጫወት ይመለከቱ ዘንድ ተጋብዘዋል። እስከ አሁን በመጣበት መንገድ የወቅቱ ዓርአያችን አድርገን የመረጥንህ ወጣት ወርቅነህ እናኮራብሃለን፣ አናከብርሃለን፣ እንወድሃለን፣ በርታ። https://www.youtube.com/watch?v=jDXiMaeozRg
Add a Comment