community best parent
of the season
Serkalem Fasil
Reason for choice is:
ታላቋ ሠርክዓለም ፋሲል የታላቁ እስክንድር ነጋ ባለቤት እና የልጃቸው ናፍቆት እስክንድር ተደናቂ እናት ናት። እነዚህ ሁለት ወላጆች ከሃያ ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ በሚያደርጉት ያልተቋረጠ ትግል ምክንያት ሠርክዓለምና እስክንድር የወላጅነት ሚናቸው እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ ሆኗል። የሁለቱ ወላጆች ህይወት ለእናት ሃገራቸው ሕዝብ ሃሳብን በነፃነት ለመግለፅ ሲባል የሚከፈል ዋጋ መሆኑ ለናፍቆት አስተዳደግና ትዳራቸው በፍፁም ምቹ አልሆነም። እንደሚታወቀው ሠርክዓለም በእስር ቤት እንድትወልደው ተደርጋ የወለደችውን ልጅዋ፣ ናፍቆትን፣ የምታሳድገው ብቻዋን ነው። ይሁን እንጂ ለባለቤቷና ልጅዋ ያላት ፍቅር፣ ክብርና ፍፁም መስዋዕትነት በምን ያህል አይበገሬ የመንፈስ ጥንካሬና የአዕምሮ ብስለት ይዛ የምትኖር ሴት እንደሆነች ይታወቃል።
ሠርክዓለም በአንድ በኩል በባለቤቷ የትግል ህይወት ውጣውረድ ምክንያት ባልተቋረጠ ዕለታዊ የስሜት ውቅያኖስ ውስጥ ትኖራለች። በሌላ በኩል በዛሬይቱ አሜሪካ ብቻዋን ስኬታማ ልጅ የማሳደግ ፈተና ውስጥ ትኖራለች። በማህበራዊ ኑሮ፣ ሴትነትና ሙያዊ ህይወቷ ውስጥ በየዕለቱ የሚከሰቱትን ተግዳሮቶችን ተቆጣጥሮ ጤናማና ደስተኛ ወላጅ መሆን ከባድ ዕለታዊ ፈተና ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። ታላቋ ሠርክዓለም ግን ዛሬም ቢሆን የማይሰበር መንፈሷና ብሩህ አዕምሮዋ ናፍቆትን በመልካም ይዞታ በማሳደግ ላይ ትገኛለች። ስለዚህ ይህ መድረክ ሠርክዓለም ፋሲልን በምርጥ ወላጅነትሽ እንወድሻለን እና እናከብርሻለን ማለትን ይፈልጋል። በርቺልን። ለከፈልሽው ዋጋ ሁሉ ከልብ እናመሠግንሻለን።
Add a Comment