የወቅቱ የማህበረሰባችን ምርጥ ተነባቢ መፅሃፍ (Community Recommended Book
of the season)
በራራ - ቀዳሚት አዲስ አበባ
(1400 - 1887ዓ.ም.) እድገት፣ ውድመት እና ዳግም ልደት
ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ
(1400 - 1887ዓ.ም.) እድገት፣ ውድመት እና ዳግም ልደት
ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ
ይህ መፅሃፍ የተመረጠበት ምክንያት: የዛሬው ትውልድ የተለያዩ አገራዊ አንድነትን ለሚቃረኑ ሃሰተኛ ታሪክና ትርክቶች የተጋለጠ በመሆኑ ይህ መፅሃፍ ግን እጅግ አስፈላጊና ሃቀኛ ታሪክን ለትውልዱ በሚያስገርም መልኩ የቀዳማዊት አዲስ አበባን ታሪክ በማስረጃ ያቀርባል። ይህ መፅሀፍ ዛሬ በኢትዮጵያ የጎሳ ብሔርተኛ ኃይሎች ያመጡትን የአዲስ አበባ ከተማን የባለቤትነት ጥያቄ በልዩ ዓይን ለማየትና ለመመርመር ይረዳል። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን በጣም በሚደንቅ ደረጃ በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጀ ታሪካዊ መፅሃፍ፣ “ያልተነገረው የኢትዮጵያ ታሪክ” በሚል እንደ አዲስ ታሪካዊ ማስረጃ በመውሰድ ስለ አዲስ አበባ ከተማ ታሪክ የራሱን ግንዛቤና ድምዳሜ ያገኝበታል። ደራሲው፣ ዶክተር ሃብታሙ መንግሥቴ፣ ይህን ታላቅ ታሪካዊ ማስረጃ የሆነ መፅሃፍን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሲያበረክቱ ለወቅታዊ ፈተናዎቻችን መፍትሔ ለማበርከት ስለሆነ ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋል።
Add a Comment