Community moral & ethical person
of the season
Abune PETROS
Reason for choice is:
YouTube: Source: By Hulu Sport – “Who was Abune Petros?” 10:56 min long https://www.youtube.com/watch?v=cCGJwI1tXj8
ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ እጅግ ታላቅና ህያው ጀግና ከሚባሉ ኢትዮጵያውያን መካከል አንዱ ናቸው። በመንፈሳዊ ህይወት መሪነታቸው ብቻ ሳይሆን በዓለማዊና ሃገራዊ ህይወትም ውስጥ ጭምር ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያሳዩት የሁለንተናዊ መሪነት ብቃት በታሪክ ከፍተኛ ደረጃ ይዞ የተቀመጠ ምሳሌነት አለው። የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ስኬታማነታቸው በወቅቱ ሠፍኖ ለነበረው የጠላት ኢጣሊያ ወራሪ ኃይልና በሕዝቡ መሃል ለነበሩ ባንዳዎችና ደካማ ዜጎች የሞራልና የሥነምግባር ዝቅጠት ፍቱን መድሃኒትነት ስለነበረው ነው። አቡኑ በህይወታቸው የከፈሉት ዋጋ በኢጣሊያኖች ለተለመኑበት የግለሰባዊ ብልፅግና የጠላት የድለላ ስጦታ ንቀትን ያሳየ ነበር። ትክክለኛ መሪ እራሱን ለማዳንም ሆነ ለመጥቀም የሚመራውን ሕዝብ ክፉ ጊዜ መጣ ብሎ አይክድም። በመሠረታዊ ዕሴቱና ማንነቱ ላይ ፅናት አለው። ምንጊዜም የሞራልና የሥነምግባር ልዕልናውን ከፍ አድርጎ እስከመጨረሻው ይጓዛል። አቡነ ጴጥሮስ ዛሬ በህይወት ቢኖሩ አንዳንድ የዘመናችን መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ መሪዎች የሚሰጡትን የወረደ የሞራልና ሥነምግባራዊ አመራር የሚፀየፉትና የሚታገሉት ነው ብሎ ይህ መድረክ ያምናል። ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ዕውተኛ የአምላክም የሕዝብም አገልጋይ ነበሩ። ትናንትም ዛሬም ደግሞ ኢትዮጵያዊ የሞራልና ሥነምግባራዊ ከፍታን በጥራት ያሳዩ መሪ ናቸው። ይህ መድረክ የወቅታችን ትውልድ የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሥራና አመራር ያስታውስ ዘንድ የወቅቱ ምርጥ ዜጋ አድርጎ ወስዷል።
Add a Comment