Debate Ethiopia – January2024
በዚህ ወቅት ከቀረቡት ሁለት የተቃርኖ ሞጋች ሃሳቦች የአመኑበትን አንዱን ኃሳብ ወይም ግላዊ አቋም ብቻ ይምረጡ። ቀጥሎም የመድረኩ መተዳደሪያ ደንቦችና ህግጋቶችን በመከተል በአመክንዮ፣ ሳይንሳዊና ታሪካዊ ማስረጃ ላይ የተደገፈ ሥነምግባራዊና ከፍተኛ የሃሳብ ተነባቢነት ጥራት ያለውን አሳማኝ ሙግቶን በኢ ሜይል በዚህ ወር (December 2023) ውስጥ ብቻ ይላኩልን።
በኢ ሜይልዎ ከሁለቱ የተቃርኖ የሞጋች ዓይነት የትኛውን ዓይነት በማያሻማ መልክ እንደመረጡ በግልፅ ያስቀምጡ። ይህ ማለት በአንድ ኢ ሜይል ሙግት ላይ ሁለቱንም አቋም ይዞ መሟገት አይፈቀድም ማለት ነው።
ከዚያም ከ3 ፓራግራፍ ያላነሰና ከ 5 ፓራግራፍ ባልበለጠ በአመክንዮ፣ ታሪካዊና፣ ሳይንሳዊ ማስረጃዎች ላይ የተመሠረተ ሥነምግባራዊ ጥራቱን የጠበቀ የፅሁፍ ሙግት በኢ ሜይል ይላኩልን። በወቅቱ ከላኩልን ለአንባቢያን ለብዙ ሳምንታት በዚህ መድረክ በማቆየት እናሳየዋለን። መድረኩ ከሌሎች ሞጋች ወገንዎችዎ ሙግት ጎን ለአንባቢያን ይቀመጣል። አንድ የሙግት ሃሳብ ላይ እስከ 3 ጊዜ ድረስ ብቻ አከታትሎ ለተቃርኖ ሞጋች መልስ መስጠት ይቻላል። የእርስዎንም ሁልጊዜ በአንድ ጊዜ ከ1ገፅ (3-5 ፓራግራፍ) ባለበለጠ ተፅፎ የተላከውን የሙግት ሀሳብ እስከ 3 የተለያዩና ተከታታይ ጊዜ ያህል ይነበባል። በቀጣዩ ወር (January 2024) ቢያንስ ለ30 ቀናት ሙሉ በዚህ መድረክ ተነባቢ ይደርግልዎታል።
በቀጣዩ ወር (February 2024) ደግሞ፣ እንደገና ለሌላ አዲስ የሙግት ሃሳብ ወይም ርዕሶች ላይ ይሳተፉልን። በተጨማሪም፣ በሶስቱም የሙግት ክፍሎች የሚሆኑ የሙግት ርዕስ መሆን ይችላሉ የሚሉትንም ሃሳብ ይላኩልን።
የቀደሙና ወይም የአላፊ ወራት ሙግቶች ለአንባቢያን በመድረኩ ይቀመጣሉ። መልካም ሙግት!
የመርህ፣ ወይም ዕሴት፣ ወይም ዕውነታ የፅሁፍ ሙግት ሊልኩልን ሲፈልጉ በሚከተለው ኢ ሜይል አድራሻ የአጠናካሪ ወይም የተቃርኖ ሙግትዎን ይላኩልን።
Our Email address is: debate@upliftingourselves.com
Please choose either you are going to make a Constructive or Affirmative Argument (AA) to the proposed Debate Ethiopia Argument Statement (DEAS) or make a Contrary Argument (CA) against the DEAS. As a rule, it is not allowed to argue or support both sides of the issue in the same email page. You are required to be 100% on one side only.
It is very important to respect and abide by the rules and meet the expected positive characteristics of the platform. Your argument ought not to be intelligible, unethical, immoral and poor quality.
One can submit his or her argument up to 3 different times consecutively via email to complete the debate. Each no more than a page (Maximum of 5 paragraphs only). Emailed debates are only displayed if they reach the platform in a timely manner. Current month Debate submissions are to be displayed on the upcoming month, for 30 days or so only. After that it will be archived, but still available for platform visitors.
Have a wonderful Debate!
POLICY DEBATES HERE
የመርህ ሙግት፥
በኢትዮጵያ ሰፍኖ የሚገኘው ቋንቋና ጎሣን መሠረት በማድረግ ውስጣዊ የአስተዳደር ግዛቶችን በጥቂት ትላልቅ ብሔሮች ብቻ የከፋፈለው የብሔር ወይም ጎሣ ህገመንግሥት በዓለማችን ልዩ የሆነ የሃገራዊ አስተዳደር የሙከራ ዓይነት በመሆን ላይ ሲገኝ ከሠላሣ ዓመታት በላይ ሆኗል። ይህ የሰላሣ ዓመታት በላይ ሙከራ ሕዝባዊ መስተጋብርንና ፍትሃዊ እኩልነት ላይ ተመሠረቶ የጋራ ጥቅምና ዕድገትን ለሁሉም የአገሪቱ ዜጎች ካለ መድልዎ ማምጣት አልቻለም የሚሉ ድምፆች ዛሬ በብዛት ይሠማሉ። ይህ ብሔሮችን እንጂ ዜጎችን መሠረት የማያደርግ የብሔር የበላይነት ዕሳቤ ለሀገራዊ ሰላምና ፍትሃዊ ዕድገት የማያቋርጥ ቀውስና ጥፋትን ማስከተሉ በተጨባጭ ስለታየ በአስቸኳይ ይህ መርህ ሊወገድ ይገባል ይላሉ። ሁለተኛው አካል ግን፣ እንደ አገራዊ መርህ ህገመንግሥቱ ለ12 የጎሳ ማንነቶች ቋንቋና ባህላዊ ዕድገትን በክልላዊነት ደረጃ ስለሚያረጋግጥ መቀጠል አለበት ይላሉ። ለተመረጡም 12 የብሔር የክልሎችን ተጠቃሚነትን፣ የፖለቲካ ሥልጣን ክፍፍልን በክልላዊ መብት ስር እንዲደራጁና የራስ ገዝ አመራር መብት እንዲኖራቸው አስችሏልና እንደ አገራዊ መርህ እንዳለ መቀጠል ያለበት አስፈላጊ ህገመንግስት ነው ይላሉ። እርስዎ ከሁለቱ ከየትኛው አካል ጋር ይስማማሉ? ለምንና እንዴት? ሌላ የተሻለ አማራጭና ምትክ የሚሉት ሃገራዊ የአስተዳድር ዓይነት የቱ ነው ይላሉ። ስለመደራደርስ ምን ያስባሉ?
VALUE DEBATES HERE
የዕሴት ሙግት፥
ከመቸውም ጊዜ ሁሉ በበለጠ ዛሬ በኢትዮጵያ ሠላም እና ፍትሕ ሁለት እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ ማህበራዊ ዕሴቶች ናቸው። ለምሣሌ ያህልም ለዘለቄታዊ መፍትሔ ፍለጋ ሲባል ኢትዮጵያዊ ማህበረሰቡ በንፅፅር ከሁለቱ ለአንዱ ዕሴት ብቻ ቅድሚያ እንዲሰጥ ከተገደደ ግን በመጀመሪያ ሊሠራበት የሚገባው ዕሴት ከሁለቱ የትኛው ነው፧ ሠላም ወይስ ፍትሕ? ለምን እና እንዴት? ከሁለቱ የትኛው ዕሴት ቅድሚያ ትኩርትና ሥራ ተሰጥቶት ቢሰራበት ማህበረሰቡ ይጠቀማል ይላሉ? ሠላም ወይስ ፍትሕ?
FACT DEBATES HERE
የዕውነታ ሙግት፥
በኢትዮጵያ የመጨረሻው የ2007 የህዝብና ቤት ቆጠራ የዜጎችን የቁጥር ብዛት በጎሳ ማንነት ለይቶ ቆጥሯል። ከነታማኝነት ችግሮቹም ቢሆን በኢትዮጵያ የመጨረሻው የ2007 የህዝብና ቤት ቆጠራ የኦሮሞ ጎሳ ማንነት ያላቸውን ዜጎች ቁጥርን በ34.5% በብዛቱ ከኢትዮጵያ አንደኛ አድርጎ አስቀምጦታል። በሌላ በኩል የአማራን ጎሳ ማንነት ያላቸውን ዜጎች ቁጥርን በብዛቱ በሁለተኛ ደረጃ 26.9% ብሎ አስቀምጦት አልፏል። ሆኖም ግን ዛሬ በኢትዮጵያ ያንን ቆጠራና ደረጃ ዕውነታ ብለው የማይቀበሉና የማያምኑ ይልቁንም፣ በተቃራኒው የአማራን ጎሳ ማንነት ያላቸውን ዜጎች ቁጥርን በብዛቱ ከኢትዮጵያ አንደኛ ነው ብለው የሚሞግቱ ዜጎች አሉ። በእርስዎ ዕይታ ወይም ግምት ደረጃው ምንድን ነው? ይህ ሙግትና ትርጉሙ ለምንና አንዴት አስፈላጊ ነው ብለው ያምናሉ?
POLICY DEBATES HERE
POLICY Debate:
According to some, the current Ethiopian ethnic federalism's constitution that divisively carved the nation in terms of only 12 "select" tribes and their languages only has so far proven to be disastrous, so urgently needs change. Others believe the constitution just needs the right application, and it is just fine as a national policy. As a national policy experiment of the Ethiopian people, which of the two arguments you support? why and why not the other argument?
VALUE DEBATES HERE
VALUE Debate:
Today both Peace and Justice are critically important values to the Ethiopian society. If society must prioritize on tackling one of these 2 values first over the other, which of the 2 values should be dealt with first? Why and how? Please explain and support your argument with examples.
FACT DEBATES HERE
FACT Debate:
As tribal population size goes, the last Ethiopian Census (in 2007) with all its credibility issues stated that the Oromo as the most populous people (34.5%) in Ethiopia. And the Amhara were placed as second most populous (26.9%) tribes in Ethiopia. However, in the absence of any credible census data since 2007, many dispute the last census as well as existing assumptions and put the Amhara simply as the most populous tribal group in Ethiopia. Which argument sounds factual? What are the relevant facts in your view and why is this argument important to you or the nation?