Page 7

ክፍል 2፥ የመካከለኛው አንድ ሺ ዓመታት (1AD – 1000 AD)

የእስከ አሁኑ የቁፋሮ ግኝቶች እንደሚያሳዩት፣ በአክሱምና በቀይ ባሕር መካከል በነበሩት ዋና ዋና ከተሞች ውስጥ የሚገኙት አብያተ ክርስቲያን የተሠሩት፣ 4ኛው እስከ 6ኛው መክዘ ባለው ጊዜ ውስጥ እንጂ ከዚያ በፊት አይደለም። የአዱሊስ ባዚለኮች (ባለ አዳራሽ አብያተ ክርስቲያን) የኩሃይቶ አብያተ ክርስቲያንና ወደ ባዚሊክ የተቀየረው የየሃ ቤተ መቅደስ፣ (እነዚህ ሁሉ) አዲሱ ሃይማኖት በዚያን ጊዜ በቀይ ባሕር ማዶ ተንሰራፍቶ ለነበረው መንግሥት እጅግ ጠቃሚ በሆኑት ቀበሌዎች ውስጥ እንደተስፋፋ ያረጋግጣሉ። 23 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

523 –525 AD አክሱም ከቁስጥንጥንያ ጋር በመስማማትና በንጉሠ ነገሥት ዩስቲንያን ባሕር ኃይል በመታገዝ ደቡብ ዓረቢያን ይይዛል። በካሌብ፣ ሌላው ስሙ እለ አፅብሃ፣ ዘመነ መንግሥት የተፈፀመው ይህ የአክሱም ወረራ፣ ከፖለቲካዊ ዓላማው አንፃር ሲታይ፣ በደቡብ ዓረቢያ አይሁዳዊነትን እያስፋፋ ክርስቲያኖችን ያሳድድ በነበረው የአካባቢው ገዥ ኑዋስ ላይ ያነጣጠረ ነበር። ናግራን ላይ ክርስቲያኖችን መጨፍጨፍ የተጀመረው፣ የመጀመሪያው የአክሱም ወረራ 523 ዓ።ም ድል ሆኖ በተመለሰ በዓመቱ ሳይሆን አይቀርም። ካሌብ በመሸነፉ ተስፋ ሳይቆርጥ እንደገና 525 የከፈተው ሁለተኛው ዘመቻ፣ አፍሪካዊው ሠራዊት ፍፁም ድል አድራጊነት ሊደመደም ችሏል። ከዚህ ድል በኋላ፣ የቀበሌው ገዥ የነበረው አብርሃ ኃይሉን በማጠናከር ከአክሱም ሥልጣን ውጭ ሁኖ ለካሌብ ግብር በማግባት ብቻ ተወስኖ ነበር።  24 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

እንደዚሁም የክርስትና መግባት አክሱምን የሥነ ጽሑፍ ዕድገት እንዳዳበረው መግለፅ ተገቢ ነው። 5ኛውና 7ኛው መክዘ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ አንዳንድበአመዛኙ በግሪክኛ የተፃፉ ሥራዎች ተተርጉመዋል። በዚህ ወቅት መጽሐፍ ቅዱስ፣ ሃይማኖታዊ ጥናቶች፣ ሕግጋተ ገዳም፣ የፍፃሜ ዓለም ትንቢቶችና ብዙ የአዋልድ ሥራዎች ወዘተ ወደ ግዕዝ ተተርጉመዋል።      26 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

አፄ ካሌብ በዓረብ ባሕረ ሰላጤ ላይ ጣልቃ እንዲገባና አብርሃምም ነፃነቱን እንዲያውጅ የገፋፉት ኤኮኖሚያዊ ምክንያቶች፣ የእምነት ወገኖቻቸው የሆኑትን የባሕረ ሰላጤውን ክርስቲያኖች ለመርዳት አፍሪካውያኖቹን ካነሳሷቸው ፖለቲካዊ ምክንያቶች ያላነሰ ክብደት የሚሰጣቸው ናቸው። ቁስጥንጥንያም አክሱምም በዓረብ ባሕረ ሰላጤ፣ ማለት መሃከለኛውን ባሕር ከሕንድ ዕውቅያኖስጋር በሚያገናኘው የንግድ መስመር ላይ እያደገ የመጣውን የፋርስን ተፅዕኖ ለመገደብ ይፈልጋሉ። ይህንን የዕጣን ጎዳና ተብሎ የሚታወቀውን፣ ለአክሱምም ከመልካ ምድራዊ አቀማመጡ የተነሳ የሞት ሽረት ጥቅም የሆነውን፣ የንግድ መስመር ለመቆጣጠር በቁስጥንጥንያና በፋርስ መካከል የተካሄደው ትግል፣ በፋርስ ድል አድራጊነት ተደምድሟል። በቀይ ባሕር ቀበሌ ውስጥ የነበረውን ተሰሚነትና የንግድ መስመር ተቆጣጣሪነት በፋርስ የተቀማው አክሱም፣ መተኪያ ከማይገኝለት የኃይል ምንጩ ተነቀለ። 25 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

570 AD በዛሬይቷ ሳውዲ አረቢያ አዲስ መንፈሳዊ ዕምነት የሆነውን የእስልምና ሃይማኖት ይዘው የሚመጡት ነብዩ መሃመድ በመካ መዲና ተወለዱ። ነቢዩ መሃመድ በተወለዱ ከአርባ ዓመታት ገደማም በኋላ፤ ነቢዩና ተከታዮቻቸው የአዲሱን የእስልምና ዕምነት አስተምህሮ በመላው ዓረቢያ ምድርና አካባቢው አሰራጩ። በአካባቢው የሳሳንያንና የባይዛንቲን ኢምፓየር የግዛቶች ውድቀትና ማነስ የጀመረው ከቀዳማዊው የእስልምና ሃይማኖት መስፋፋት ጋር በተያያዘ ያልተቋረጠ ዘመቻ ነበር። 

615 በዓለም አዲስ በተወለደው የቅዱስ ነብዩ መሐመድ የእስልምና ሃይማኖት አስተምህሮ ምክንያት የመጀመሪያው የሙስሊም ሂጅራ ተደረገ። ይህም የሆነው በዛሬይቱ ሳውዲ ዓረቢያና አካባቢው በአዲሱ የእስልምና እምነትና ተከታዮች ላይ በሚደርስባቸው የህልውና አደጋ ምክንያት ነበር። ይህ ሂጅራ በመባል የተከሰተው የወደ ኢትዮጵያ ስደት ሃሳብ የመጣው፣ ከራሱ ከቅዱስ ነብዩ መሐመድ እንደሆነም በታሪክ ተቀምጦ ይገኛል። በመካና አካባቢው ለጭፍጨፋ አደጋ ተጋልጠው የነበሩትን፣ ነብዩ በዚያ ሊያድኗቸው ስለማይችሉ፣ ነገርግን በኢትዮጵያ ፍትሐዊና ፈርሃ እግዚአብሔር ያለው የክርስቲያን ንጉሥ ስለሚገኝ ተከታዮቹንና ያራሳቸውን የቤተሰብ አባላት ጭምር እዚያ ብትሔዱ ትድናላችሁ አሏቸው። በዚህም መሠረት 11 የሚሆኑት ወደ አትዮጵያ መጡና የተባለው ሁሉ ሆነላቸው።

616 ከዚያም ዓመት ገደማ እነዚህ 11 በኢትዮጵያ በሰላምና በነፃነት አዲሱን ሃይማኖታቸውን ይዘው እያመለኩ እንደቆዩ፣ ሁለተኛው ሂጅራ ተከሰተ። ዳግምም ለሁለተኛ ጊዜ በስኬት በሃይማኖታቸው ምክንያት የተደረገው ከመካ የወደ ኢትዮጵያ ስደት (ሂጅራ) 83 ወንዶችና 18 ሴቶችን ያካተተ ቡድን ነበር። ሆኖም ግን በመካ የእስልምና ሃይማኖትና ለማጥፋት በኃይላቸው ሥልጣንን የያዙ ቋራሺዎች ይህን ባስተዋሉ ጊዜ፣ ይህን የሂጅራ ክስተት ለማስቆም ወደ ኢትዮጵያው ንጉሥ ለመሄድ ተገደዱ። ቋራሺዎች ሄደውም ንጉሡን እነዚህ በኢትዮጵያ በሰላምና ነፃነት እየኖሩ አዲስ ሃይማኖታቸውን እያመለኩ የሚኖሩት ዜጎቻችንን መልሳቸው ወይም እኛ ወደ አገራቸው እንድንመልሳቸው ስጠን ሲሉ ብዙ ወርቅና እጅ መንሻ ይዘው ጠየቁት። ጨምረውም ንጉሡን የአንተን የክርስትና ዕምነት ተፃፃሪ ዕምነት እንዳላቸውም ነገሩት።


በወቅቱ አክሱም የተቀመጠው የኢትዮጵያ ንጉሥ ግን ነብዩ መሐመድ እንዳሉት፣ ፍትሐዊና ፈርሃ እግዚአብሔር ያደረበት በመሆኑ የራሱን ምርመራ በማድረግ ወሰነ። በሂጅራ ከመጡት ውስጥም አስጠርቶ ስለ አዲሱ የእስልምና ሃይማኖታቸውና ስለአንድ አምላክ ዙሪያ ያለውን ሁሉ በመጠየቅ ከዓረቢያ በመጡ ከሳሾቻቸው ፊት መረመራቸው። በመጨርሻም ፍርዱን ሠጠ። ፍርዱም እናንተም ሆነ የእስልምና ሃይማኖታችሁ በኢትዮጵያ እስከፈላጋች ሁበት ጊዜ ድረስ በሰላምና ነፃነት መኖር ትችላላችሁ አላቸው።  ምንም ያህል ወርቅ ቢሰጠኝም እንኳን አሳልፌም አልሰጣችሁም አላቸውና በሰላም ኑሩአቸውን ቀጠሉ። በንጉሡ ግዛት ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀምሪያዎቹ የሃይማኖት ስደተኞች ሆነው አዲሱ ሃይማኖታቸውን ይዘው በሰላም ኖሩ። በዛሬይቷ ትግራይ ምድር የሚገኘው አል ነጃሺ መስጊድ የዚህ ታሪክ አካል በመሆንም ላይ ይገኛል።  

በ615 ገደማ በስደተኞቹ ተቆርቁሮ በየዘመኑ እየታደሰ የተገነባው የመጀመሪያው የእስልምና ሃይማኖት መስጊድ ወይም ቤተ ዕምነት በኢትዮጵያ።

undefined

  Masjid al-Najāshī (مَسْجِد ٱلنَّجَاشِيCoordinates13°52′32.0″N 39°35′55.3″E   ምስል፣ ከዊኪፒዲያ የተወሰደ።

 

የአክሱም ውድቀት፤ 

650-750 AD ከዚያ ለአክሱም ጎጂ ከሆነው ክስተት በኋላ፣ 7ኛውና 8ኛው መክዘ ውስጥ የእስላም ተሰሚነት እያየለ ሄደ። መሐመዳውያኑ በፋርስ ግዛት ውስጥ ተደጋጋሚ ዘመቻና ወረራ በማካሄድ ይህን መሃከለኛውን ባሕር ከሕንድ ዕውቅያኖስ ጋር የሚያገናኘውንና እጅግ ጠቃሚ የሆነውን የንግድ መስመር ከእጃቸው አስገቡ። 7ኛው መክዘ ፍፃሜና 8ኛው መጀመሪያ ላይ የዳህላክ ደሴቶችንና የምፅዋን ወደብ በመያዝ፣ በአፍሪካ የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ አቋማቸውን አጠናክረው በአክሱም መንግሥት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሱ።   

ከውጫዊው የኃይል ሚዛን መለወጥ ጋር በተያያዘ ኤኮኖሚያዊ አቋሙና በግዛታዊ ይዞታው የተዳከመው መንግሥት፣ ይህም በበኩሉ መገመት እንደሚቻለው ሁሉ የማዕከላዊ ሥልጣን መዳከምን ያስከተለበት መሆኑ አልበቃ ብሎ፣ የመጨረሻ ግብዓተ መሬቱን ያመጡ የከባድ ውስጣዊ ነውጦች አውድማ ይሆናል። 

ከባሕር ጠረፍ የተገፈተረው የዚህ መንግሥት ሕዝብ፣ ሥልጣኔውንና ቋንቋውን ይዞ ይበልጥ  ወደ ደቡብ ዘልቆ በመግባት ለክርስትና አዲስ መሬት ያቀናል። ቀደም ባለው ጊዜ ከደቡብ ዓረቢያ ፈልሰው የመጡት  ሰፋሪዎች በሥፍራው ከነበረው ልዩ ልዩ ማህበረሰብ ጋር ጥምረት ሲፈጥሩ እንደሆነው ሁሉ፣ አሁንም ይህኛው በስፍራው ከአገኘው ሕዝብና ከሥልጣኔው ጋር ይቀላቀላል። ይህ ለምዕተ ዓመታት ግዜ የዘለቀው ያላቋረጠ የሕዝቦችና የባሕሎች ውህደትና ትስስር ነው፣ ለኢትዮጵያው ሕዝብ ማንነትና ሥልጣኔ ዛሬ ያለውን ልዩ ገፅታና ባሕርይ ያላበሰው።  26፣ የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

ከቁፋሮ ግኝቶችና ከዓረብ ባለታሪኮች ሥራዎች ለመረዳት እንደሚቻለው፣ በጊዜው ንጉሥ ኤዛና ድል አድርጎ ያባረራቸው የቤጃ ነገዶች፣ 8ኛው መክዘ አካባቢ ላይ በሰሜንና በባሕር ጠረፍ ግዛት ዘልቀው ገብተው ነበር። ይህ ወረራ ያለ ጥርጥር አክሱም መዳከም አስተዋጽዖ አድርጓል። ማንነቷ ያልታወቀውና አረማዊቷ ንግሥት፣ 9ኛውና 10ኛው  መክዘ ውስጥ ተደጋጋሚ ወረራ በማድረግ አክሱምን ለመጨረሻው ያሰናበተችው ከዚህ በኋላ ነው። 28 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

ከዚህ የሚከተለው አረማዊቷ በሚል ስለተጠቀሰችው ንግሥት ኢትዮጵያዊ ትውፊቱ ያስቀመጠው ነው።  

በጥንት ጥንት ዘመን፣ ይላል ተያይዞ የወረደው የኢትዮጵያው ትረካ፣ ቁጥራቸው በርከት ያለ እስራዔላውያን ካህናት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሕዝቡን ስለ ብሉይ ኪዳንና ስለማያውቀው አምላክ አስተማሩት። እነዚህ ፍሬሜንቱስ (አባ ሰላማ) መጥቶ የአክሱምን መንግሥት  ወደ ክርስትና እስከ መለሰበት ጊዜ ድረስ ከሕዝቡ ጋር ተዋልደው ከዚሁ ኖሩ። ግን አዲሱን እምነት የተቃወሙ ሁሉ ከአክሱም ተባረሩ። እነዚህ ተባራሪዎች በስሜን፣ በወገራ፣ በወልቃይትና በላስታ ሠፈሩ። ስለዚህ ፈላሻ ተብለው ይጠራሉ። ፈላሻ ማለትከውጭ የገባተንከራታችእንደ ማለት ነው። በመጨረሻም ለሰው አስቸጋሪ የተፈጥሮ ምሽግ የሆነውን የሰሜንን ተራራማ አገር አገራቸው አድርገው ለዘለቄታው ሠፈሩበት። ከዚያም ቀስ በቀስ ኃይል አግኝተው፣ ጌዴዎን የተባለ ንጉሥ ለመምረጥ በቅተዋል። 27 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

841 AD የአክሱም መሪ ደግናዠን ሙቶ ልጁ አንበሣ ውድም ገና ህፃን ሆኖ አልጋ ያዘ። በዚህን ጊዜ ከላስታ ፈላሾች ውስጥ ጌዴዎን የተባለ መሣፍንት፣ ጉዲት ወይም አስቴር የተባለች እጅግ ውብ ልጅ ነበረችው።

842 AD ቆንጆዋ ጉዲት ይህን እንደሰማች፣ የስሜንና የላስታ ወገኖችዋን አስከትላ አክሱምን ለመያዝ ዘመተች። የአክሱም ልዑላን አልጋ ወራሹን ለማትረፍ ይዘውት ከትግሬ ወደ ሸዋ ሲሸሹ፣ ርህራሄ ቢሷና ፀላዔ ክርስቲያን የሆነችው ጉዲት ዙፋን ያዘች። ከ1ኛው መክዘ አጋማሽ ላይ ጀምሮ ይሆናል ለ40 ዓመታት በፍፁም ጭካኔ ገዛች። በዚህን ጊዜ አብያተ ክርስቲያንን አቃጠለች። የአክሱምን የሥዕል ቅርሶች አወደመች። እርስዋ ስትሞት በትግሬ ምድር ትልቅ ደስታ ሆነ። … ከ9ኛው እስከ 10ኛው መክዘ ባለው ጊዜ ውስጥ በቀውስ ላይ የነበረውን የአክሱምን መንግሥት የመታው፣ በትውፊቱ ዮዲት በሚል ተይዞ ዝንተ ዓለሙን ሲዘከር የሚኖረው ይኸው የዛግዌ ኃይል ሳይሆን አይቀርም። 28 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

850 AD የውጭ ነጋዴዎች ቡናን ከፋ ከሚባለው የደቡብ ምዕራባዊ ለም የኢትዮጵያ ክፍል አገኙ። ወደ ዓረቢያ በመውሰድም ቡናን አስተዋወቁ። 

820 – 950 AD በዚህ አኳኋን አክሱም 6ኛው መክዘ ጀምሮ የውድቀት ጉዞውን ይጀምራል። ከባሕር ጠረፍ ተገፍቶ ያፈገፈገው መንግሥት የነበረው አማራጭ ወደ ደቡብ መስፋፋት ብቻ ነው። 9ኛው መክዘ ላይ፣ ናዝሬት በመውደቅ ላይ ያለው መንግሥት መንበረ ፓትሪያርክ ሆነች። … በመጨረሻም 8ኛው መክዘ ፍፃሜና 10ኛው መጀመሪያ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ፣ የቀድሞው መናገሻ ከተማ የተራቆተ ባድማ ብቻ ሊሆን በቅቷል። 25 የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ከመጀመሪያው እስከ አሁኑ ዘመን፣ ባርትኒስኪ እና ማንቴል፡ኒየችኮ፣ 2003

 

 Page 7 – END  

Comments are closed.